
አዲስ አበባ: ግንቦት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የታዛቢነት ሚና እንደነበራቸው ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ገነት ስዩም ሴቶች በመራጭነትም ኾነ በታዛቢነት የነበራቸውን ተሳትፎ በጥንካሬ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በምርጫው ያጋጠሙ ጥቃቅን ችግሮችን ለመፍታት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የወሰደው ፈጣን እርምጃም የሚደነቅ እንደነበርም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
ኅብረተሰቡ እስከ ሌሊት 6 ሰዓት ድረስ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ ኾኗል ነው ያሉት።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ከ14 ሺህ በላይ ታዛቢዎችን በማሠማራት ከ25 ሺህ በላይ ምርጫ ጣቢያዎችን መታዘብ እንደተቻለ በመግለጫው ተነስቷል።
#አሚኮ #አሚኮ_ዜና #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ #ምርጫ
ዘጋቢ፦ ሰላማዊት ነጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
