
ጎንደር: ግንቦት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 32ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የምርምር ጎባኤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር)፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አሥራት አጸደወይን (ዶ.ር)፣ የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ጉባኤውን የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አሥራት አጸደወይን (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው በጤናው እና ሌሎች ዘርፎች በቴክኖሎጅ የታገዘ የምርምር ተግባር እያከናወነ መኾኑን አንስተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ባሻገር የማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እየሰጠ ነውም ብለዋል።
የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያወጧቸው ምርምሮች የማኅበረሰብን ችግር መነሻ ያደረጉ ሊኾኑ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ምርመምሮች ከቴክኖሎጅ ጋር የሚጣጣሙ ሊኾኑ ይገባልም ነው ያሉት።
ምርምሮች የዲጂታል 2030ን ግብ እውን የሚያደርጉ እና የሚያግዙ ሊኾኑ እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ናቸው።
የሚሠሩ ምርምሮች ወደ ተግባር የሚቀየሩ እና የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈቱ መኾን እንዳለባቸውም አንስተዋል።
#አሚኮ_ዜና #ምርምር_”ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ:- አዲስ ዓለማየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
