
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር፣ በምዕራብ ጎጃም፣ በሰሜን ጎጃም እና በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥ ምሥራቅ ዕዝ ባደረገዉ ኦፕሬሽን 204 ተላላኪ ጽንፈኞችን በመደምሰስ 161 ማቁሰሉን ገልጿል።
በሰሜን ጎጃም ዞን የተሰማራዉ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል አዲሱ መሀመድ እንዳሉት ኢትዮጵያ ሊወራት የመጣውን ጠላት ባይደፈሬነት አሳፍራ የመለሰችና ለዘመናት ተከብራ የኖረች ናት ብለዋል። ይህችን ሀገር መንግሥት አልባ እና የተዳከመች ለማድረግ እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሳይኾን ባፈሙዝ ሥልጣን ለመያዝ ያለሙ የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ተልዕኮ ያነገቡ ባዕዳን እና ባንዳዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። እነዚህ አካላት 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ እዳይካሄድ ሕዝቡን ለመረበሽ እና ሁከት ለመፍጠር ያቀዱትን የተንኮል ሴራ ሠራዊቱ ከማኅበረሰቡ እና ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ያለ አንዳች የጸጥታ ስጋት እንዲፈጽም ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በዚህ ቀጣና 29 የጽንፈኛ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 47ቱ ደግሞ ቁስለኛ ኾነዋል። ኅብረተሰቡ ለሰላም ያለውን ጽኑ ፍላጎት እና የዘራፊውን ጽንፍኛ ተልዕኮን አንግበው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ያለውን የመረረ ጥላቻ አሳይቷል ነዉ ያሉት።
ሠራዊቱ በምዕራብ ጎጃም እና አዊ ብሔረሰብ ዞን በተሰማራንባቸዉ ቀጣናዎች በተለይም በፍኖተ ሰላም እና በቲሊሊ ከተሞች ዙሪያና በተለያዩ አካባቢዎች የአካባቢዉን ሰላምና ጸጥታ ለማናጋት አቅዶ የመጣዉን የጠላት ኃይል በጀግናዉ የኮሩ ክፍለ ጦሮች እና ስታፍ ክፍሉ እንዲሁም በጥምር ጦሩ በደረሰበት ከፍተኛ ምት ህልሙ ቅዠት ሆኖበታል ነዉ ያሉት።
በዚህ ከፍተኛ ኦፕሬሽን በጽንፈኛው ላይ የሰዉ ሀይል እና የቁሳቁስ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን፤ የተደመሰሰ የጠላት ሃይል 85፣ የቆሰለ 40፣ የተማረከ 01፣ እጅ የሰጠ 01 መኾኑ ተጠቁሟል። አንድ ብሬን፣ ስድስት ክላሽ፣ ሁለት የቃታ መሳርያ፣ 4 የብሬን ዝናር ከነ ጥይቱ ፣ አንድ የእጅ ቦምብ፣ ሶስት የክላሽ ካዝና እና አንድ ትጥቅ መመማረኩንም ጠቅሰዋል።
ከተደመሰሱት የጽንፈኛው አባላት መካከልም ሙሉጌታ የተባለ የፅፈኛዉ ሻለቃ አዛዥ፣ ዋሴ ወርቁ ጎድ አዛዥ፣ ጤናዉ አቻም ክፍለ ጦር አዛዥ እና የቡድን መሳርያ ተኳሾች ይገኙበታል።
በደቡብ ጎንደር ዞንም በደብረ ታቦር፣ በእስቴ፣ በአንዳቤት፣ በስማዳ፣ በሳሊ፣ በንፋስ መውጫ፣ በታች ጋይንት፣ በላይ ጋይንት እና ክምር ድንጋይ ላይ ጽንፈኛዉ ያለ የሌለውን ኃይል ከተደበቀበት ጉድጓድ አሰባስቦ የኅብረተሰቡን ሰላም ለማወክ ቢመጣም በሠራዊቱ እና በክልሉ የጸጥታ ኃይል የተቀናጀ ኦፕሬሽን ጠላት ሙትና ቁስለኛ መሆኑን የቀጠናዉ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ልጃለም ምትኩ አብራርተዋል።
በዚህ ቀጣናም በጠላት ላይ የደረሰው ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ኪሳራ ሲታይ የተደመሰሰ ጠላት 90፣ የቆሰለ 74፣ የተማረከ ክላሽ 09፣ የቃታ መሳሪያ 11 እና አንድ ጂም 3 መሳሪያ ተማርኳል።
በቀጣናው ግዳጃቸውን በአመርቂ ውጤት እየፈፀሙ ያሉት የክፍለ ጦር አመራሮች እንደተናገሩት ሠራዊቱ ጠላትን ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ለሚሰጠው ግዳጅ አስፈላጊውን ሥነ ልቦናዊ እና ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸም ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጓል ነው ያሉት። ዛሬም ነገም የሀገራችን ሰላም እና ፀጥታ ለመጠበቅ ዝግጁ ነው ብለዋል። መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
