ወደ ካናዳ የሥራ ምዝገባ እና ስምሪት ተጀምሯል?

6
ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዜጎች ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ በውጭ ሀገራት በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ በሕጋዊ መንገድ እንዲሰማሩ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።
ነገር ግን ዜጎችን ለሥራ ወደ ካናዳ መላክ አንዳልጀመረ እና ምዝገባም እያካሄደ እንዳልኾነ ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
👉ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረማ በሕጋዊ መንገድ ዜጎች ስምሪት የሚወስዱባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
✍️ሳውዲ አረቢያ
✍️የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ
✍️ጆርዳን
✍️ኳታር እና
✍️ሊባኖስ ናቸው።
⚠️ጥንቃቄ
#”ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ ካናዳ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ጀምሯል”
#”ወደ ካናዳ እንልክዎታለን” በማለት ከፍተኛ ገንዘብ ከሚጠይቁ እና
#”ከሚኒስቴሩ ሕጋዊ ውክልና ተሰጥቶናል” የሚሉ መልዕክቶች የተሳሳቱ እና የአጭበርባሪዎችና ተጠንቀቁ።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየክረምቱን መግባት ተከትሎ ከሚከሰት የወባ በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
Next articleወረታ ከተማን የማልማት ሥራ እየተሠራ ነው።