
አዲስ አበባ: ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ እንደነበረው የገለጸው የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን በተለይም ወጣቶች በታዛቢነት እና በበጎ ፈቃደኝነት መተፋቸውን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ተወካይ አሌክሳንደር ንጉሴ ተናግረዋል።
ተወካይ ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ ወጣቶች በምርጫው መሳተፋቸው ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እንዲያድግ እና ሀገራዊ ኀላፊነት እንዲሰማቸው ያደርጋል ብለዋል።
የምርጫ ሕጎች እና ሥርዓቶች እንዲከበሩም የተሰጣቸውን የታዛቢነት ኀላፊነታቸውን መወጣታቸውንም ገልጸዋል።
ፌዴሬሽኑ ምርጫ ቦርድ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የነበረውን ክንውን መታዘቡን እና በዝግጅቱ የግብዓት አቅርቦት ችግር አለመኖሩንም ተናግረዋል።
የምርጫ ውጤት በሚገለጽበት ወቅት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተረጋጋ እና ሕጋዊነትን በተከተለ መልኩ ውጤቱን መቀበል እንደሚገባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በምርጫው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታዛቢዎች የነበራቸው ክትትል የምርጫውን ተዓማኒነት የበለጠ የሚያጎላ እንደነበር ያነሳው የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን 32ሺህ 500 ወጣቶች በታዛቢነት መሳተፋቸውንም ገልጿል።
ወጣቶች ምርጫውን በገለልተኛ እና ሙያዊ ሥነ ምግባርን በተላበሰ መልኩ በመታዘብ ኀላፊነታቸውን መወጣታቸውም በመግለጫው ተነስቷል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አዲስ_አበባ #ኢትዮጽያ
ዘጋቢ ፦ሰላማዊት ነጋ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
