የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን በምርጫው ሂደት ታዘብኳቸው ያላቸው ዋና ዋና ነጥቦች 👇

29

 

📌 የመራጮች ቁርጠኝነት እና ድባብ፦

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ያለውን ትልቅ ቁርጠኝነት ያሳየበት ምርጫ ነበር። መራጮች ከማለዳው ጀምሮ በሰላማዊ እና በታጋሽነት ስሜት በሰልፍ በመቆም ድምፃቸውን ሲሰጡ ውለዋል።

📌 የጸጥታ እና የሰላም ሁኔታ፦

በአብዛኛዎቹ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እና አካባቢዎች የነበረው የጸጥታ ኹኔታ የተረጋጋ እና ሰላማዊ ነበር። ይህም መራጮች ያለምንም ስጋት ወጥተው መብታቸውን እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

📌 የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥንካሬ፦

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህንን መጠነ ሰፊ ሀገራዊ ምርጫ በበላይነት በመምራት፣ ቁሳቁሶችን በማደራጀት እና ሂደቱን በማስተናገድ ረገድ ያደረገው ጥረት የሚደነቅ ነው። በተለይም ያጋጠሙ የተወሰኑ የቴክኒክ እና የሎጂስቲክስ እክሎችን ፈጥኖ ለመፍታት የተደረጉት ጥረቶች በበጎ ጎን የሚነሱ ናቸው።

📌 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የዕጩዎች ስክነት፦

በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች እንዲሁም ወኪሎቻቸው በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያሳዩት የሰለጠነ የባህሪ ጨዋነት እና ለሕጉ ተገዢ የመሆን ስሜት ለሂደቱ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ታዛቢዎች አንስተዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ድኅረ_ምርጫ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በወርኃ ሚያዝያ እና ግንቦት ያከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራት:-
Next article“ሕዝቡ በሰጠው ድምጽ ከሚመረጠው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ ነን” የፖለቲካ ፓርቲዎች