ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ።

20

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የሥራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል። ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን ነው ያሉት።

‎ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲኾኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ሕዝቡ ለሀገሩ ድምጹን በመስጠት ያሳየው የዴሞክራሲ ፍላጎት ድንቅ ነበር” አቶ ጥላሁን ደጀኔ
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በወርኃ ሚያዝያ እና ግንቦት ያከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራት:-