“ሕዝቡ ለሀገሩ ድምጹን በመስጠት ያሳየው የዴሞክራሲ ፍላጎት ድንቅ ነበር” አቶ ጥላሁን ደጀኔ

19

 

ደብረ ታቦር: ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የላቀ ተሳትፎ ላደረጉ የዞኑ ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።

የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የደቡብ ጎንደር ሕዝብ ሀገራዊ ኀላፊነቱን በሚገባ ተወጥቷል ብለዋል።

የዞኑ ሕዝብ የዴሞክራሲያዊ አካሄድን አስፈላጊነት ጠንቅቆ የተረዳ መኾኑንም ገልጸዋል።

“የዞኑ ሕዝብ ለሀገሩ ድምጹን በመስጠት ያሳየው የዴሞክራሲ ፍላጎት እና የሀገር ፍቅር ድንቅ ነበር” ብለዋል።

ሕዝቡ ድምጽ ከመስጠት ባለፈ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ እና የምርጫ ቁሶችን ደኅንነታቸውን በባለቤትነት በማስጠበቅ ረገድ ላደረገው አስተዋጽኦ ዋና አሥተዳዳሪው አመስግነዋል።

ማኅበረሰቡ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መልካም ተሳትፎ አድርጓል፤ በካርዱ ከመረጠው እና በቀጣይ ከሚታወቀው መንግሥት ጋር በመኾን በልማት እና በዘላቂ ሰላም ግንባታ ዘርፍም ቀና ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።

#አሚኮ-ዜና #ምርጫ2018 #ደብረ-ታቦር #አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዓት የሚረጋገጠው በራስ አቅም ማምረት ሲቻል ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ።