“የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዓት የሚረጋገጠው በራስ አቅም ማምረት ሲቻል ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

10

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሀገር ሉዓላዊነት እና ነጻነት በምልዓት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው ብለዋል።

መንግሥትም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የታለመውን ዘላቂ ዕድገት እና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን አሻሽሏል ፤ አሠራሮችን ዘርግቷል፤ ማበረታቻዎችን አድርጓል ነው ያሉት።

የዚህ ሪፎርም አካል የኾነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም ፍሬው በግልጽ እየታየ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እና የምርጫ ዕድገት ሂደት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ ነው” የኢጋድ ታዛቢዎች ቡድን
Next article“ሕዝቡ ለሀገሩ ድምጹን በመስጠት ያሳየው የዴሞክራሲ ፍላጎት ድንቅ ነበር” አቶ ጥላሁን ደጀኔ