“7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እና የምርጫ ዕድገት ሂደት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ ነው” የኢጋድ ታዛቢዎች ቡድን

10

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሲታዘቡ የሰነበቱት የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ምርጫውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቀድሞ የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድን መሪ ዋዲራ ሰፔሲዎሳ (ዶ.ር) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እና የምርጫ ዕድገት ሂደት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍን የከፈተ ነው ብለዋል።

ምርጫው በርካታ አዳዲስ አሠራሮች የታዩበት ምርጫ ተብሎ ይገለጻልም ነው ያሉት። ለዚህም ምክንያቱ መጠነ ሰፊ የኾኑ ተቋማዊ፣ አሥተዳደራዊ እና የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች ሥራ ላይ በመዋላቸው እንደኾነም አንስተዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ #የኢጋድ_ታዛቢ #ኢትዮጽያ

ዘጋቢ ፦ ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየቻግኒ ከተማን ውበት እየገለጠው ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ
Next article“የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዓት የሚረጋገጠው በራስ አቅም ማምረት ሲቻል ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ