
ደብረ ብርሃን፡ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በኾነ መንገድ መከናወኑን የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡት ወይዘሮ እጥፍወርቅ ካሳዬ የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራም በመረዳት ድምፃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።
የምርጫ ሂደቱ ፍላጎታቸውን በነጻነት ያንጸባረቁበት እንደነበር የገለጹት ደግሞ መምህር ሚሊዮን መንግሥቱ ናቸዉ።
የምርጫ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ዜጎች በጸጋ በመቀበል የዴሞክራሲ ባሕልን ሊያሳድጉ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ነሲሳ አወል ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና በሠለጠነ መንገድ የተከናወነ እንደነበር ጠቁመዋል።
ምርጫዉ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ጉዞ ከፍ እንደሚያደርገዉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ ስንታየሁ ሀይሉ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
