”የድምጽ ቆጠራውን ውጤት ለመቀበል ተዘጋጅተናል” በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

13

 

ከሚሴ፡ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫን በማስመልከት ሃሳባቸውን ለአሚኮ ሰጥተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ አባል እና የብልጽግና ፓርቲ የክልል ምክር ቤት እጩ አቶ አህመድ ሁሴን በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና በድህረ ምርጫ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት ተቀራርበው ሢሠሩ እንደነበር ገልጸዋል።

በምርጫ ወቅት ችግር እንዳይፈጠር በመቀራረብ በመሥራታቸው ምርጫው በሰላም ተጠናቅቋልም ብለዋል። የዜግነት ኀላፊነታቸውን የተወጡ ዜጎችንም አመስግነዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ አባል እና የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት እጩ መሐመድ ተሾመ ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ቀድሞ የጋራ ምክር ቤት አቋቁሞ ወደ ሥራ በገባ ማግስት በርካታ ሥራዎችን ተቀናጅተው መሥራታቸውን ጠቅሰዋል።

የድምጽ ቆጠራው ተጠናቅቆ ውጤት በሚገለጽበት ወቅት ሁላችንም ውጤቱን በመቀበል አሸናፊ ለሚኾነው አካል ሁሉ የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት ለማስተላለፍ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ማኅበረሰቡም ያለምንም ከልካይ በነቂስ በመውጣት የፈለገውን አካል ሲመርጥ መቆየቱን ገልጸዋል።

ሌላው የምክር ቤቱ አባል እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የክልል ምክር ቤት እጩ ማስረሻ ገብሬ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ምርጫ መካሄዱን ተናግረዋል።

ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት በተረጋጋ ኹኔታ ይበጀኛል ያለውን መምረጥ ችሏልም ብለዋል።

ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገለጫ በመኾኑ የተካሄደውን የምርጫ ውጤት ምንም ይሁን ምን ለመቀበል መዘጋጀታቸውንም ጠቅሰዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ የፈተና መስጫ ቀናትን ይፋ አደረገ።
Next article7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ተሳትፎ እና በስኬት መጠናቀቁን የፓርቲ ተወካዮች ገለጹ።