
ደሴ: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቃሉ አንድ ምርጫ ክልል በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ አጠናቅቀው ለማኅበረሰቡ ጊዜያዊ ይፋ አድርገዋል።
ማኅበረሰቡ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ውጤቱን እየተመለከተ ነው።
የድምጽ አሠጣጥ ውጤትን ሲመለከት ያገኘነው የከተማዋ ነዋሪ ወጣት ኑሩ ሙሐመድ ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ በመጠናቀቁ ደስተኛ መኾኑን ተናግሯል።
ይበጀናል ብለን መርጠናል ነው ያለው። ውጤትን በጸጋ መቀበል ከማኅበረሰቡ እና ከተወዳዳሪ ፓርቲዎች እንደሚጠበቅም ተናግሯል።
ሌላኛው ነዋሪ ታደሰ አሊ ማኅበረሰቡ በፍትሐዊ መንገድ በነጻነት መምረጡን ተመልክቻለው ብለዋል። ለሀገራቸው ድምጻቸውን በመስጠታቸው ደስተኛ መኾናቸውን ነው የገለጹት።
አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
