“ምርጫው የዴሞክራሲ ልምምድን ያየንበት ነው” የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን

6

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሠብሣቢ የቀድሞዋ የሩዋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ዋዲራ ስፔሲዮሳ (ዶ.ር) የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ሢሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

የታዛቢ ልዑክ ቡድን መሪው ከሴቶች፣ ከወጣት አደረጃጀቶች፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር መገናኘታቸውን ገልጸዋል።

የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶችም በምርጫው ዙሪያ በርካታ ተግባራትን እንዳከናወኑ ነግረውኛል ብለዋል።

ድምጽ መስጠት ከተጀመረ አንስቶ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዕኩል ድምጽ የመስጠት ዕድል እንዳገኙ በትዝብታችን አይተናል ነው ያሉት።

እናቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሴቶች የምርጫውን ሕግ ባከበረ መንገድ መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።

ይህ ሂደትም በአፍሪካ ልናይ የምንፈልገውን “የዴሞክራሲ ልምምድ ያየንበት ነው” ሲሉ የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ሠብሣቢ ዋዲራ ስፔሲዮሳ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን ዳረጎት

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🗳️ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እየተከናወነ ነው” የደብረ ብርሃን ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
Next article“ምርጫው ከፍተኛ የሕዝብ ቁርጠኝነት የታየበት ነው”