
#ባሕር_ዳር: ሰኔ 25/2018 ዓ.ም በምራብ ጎጃም ዞን ደጋዳሞት ወረዳ ባደረገው ኦፕሬሽን 116 ጽንፈኞችን መደምሰሱን ምሥራቅ እዝ አስታውቋል።
ስምሪቱን የመሩት የኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ሬድዋን ሪባቶ እና የክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ግፋወሰን አበበ እንደተናገሩት በደጋ ዳሞት ወረዳ ሐሙስ ገብያ በተደረገ የተቀናጀ የጸረ ሽምቅ ስምሪት 86 የጽንፈኛ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ ፣ የዝናቡ ልንገረውን ሁለት አጃቢዎች ጨምሮ 30 የጥፋት መልዕክተኞች ቆስለዋል፡፡ በድምሩ 116 የጽንፈኛው አባላትን ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ነው ያስታወቀው።
በስምሪቱ ስምንት ኤ ኬ ኤም ክላሽ ፣ 68 የድሽቃ ጥይት ከነሸንሸሉ ፣ ሦስት የቃታ መሣሪያ ፣ ዘጠኝ ቦንብ ፣ ትጥቆች እና ለማወናበጃነት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የጸጥታ አካላት አልባሳት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
ቡድኑ ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ በርካታ ጥሬ እቃዎች ሲወድሙ የጦር መሣርያዎች ፣ ተተኳሾች እና ትጥቆች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
በዚህ ጥቃት ከተደመሰሱት የጽፈኛው ቡድን ሻለቃ አዋጊዎቻቸው እና የሎጀሰቲክ አመራሮች መካከል
1ኛ. ዳኘ ድሉ የሻለቃ ሎጀስቲክስ ኀላፊ የነበረ
2ኛ. ደጀን ጤና ነባር ተዋጊ
3ኛ. ምኔ አደራው ተዋጊ
4ኛ. አወቀ ይታይህ ምክትል ሻለቃ መሪ
5ኛ. አሰየ ደሴ ተዋጊ ቀበሌ ሳንቲማ
6ኛ. መንግሥቴ የተባለ የእነርሱ የመጀመሪያ ኮማንዶ ቀበሌ ጫት ወርካ ይገኙበታል፡፡
አዛዦቹ እንዳሉት በዚህ ስምሪት የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል እና የየአካባቢው ሕዝብ የራሳቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡ የዞኑን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የጽንፈኛ ኃይል በመለየት ስልታዊ ጥቃት ተፈጽሟል።
የምሥራቅ እዝ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ በላከው መረጃ እንዳመላከተው ሠራዊቱ ይህንን የሕዝብ ስቃይን ደስታው ፣ የዜጎች መጎሳቆልን ግቡ አድርጎ የሚንቀሳቀሰውን የኢትዮጵያ ከሀዲዎች ተላላኪ የመደምሰሱን ግዳጅ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
