🗳️ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እየተከናወነ ነው” የደብረ ብርሃን ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

8

 

ደብረ ብርሃን: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ ሂደቱ በከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ እና በሰላማዊ ሁኔታ እየተከናወነ መኾኑን አስታውቀዋል።

የከተማው የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እና የምክር ቤቱ ሠብሣቢ ሰለሞን ጌታቸው እንደገለጹት ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ እንዲኾን አስቀድሞ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች ተደርገዋል። በዚህም ምክንያት ያለምንም የጸጥታ ችግር የተሳካ ምርጫ ማካሄድ መቻሉን ገልጸዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ እና የምክር ቤቱ ምክትል ሠብሣቢ ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ በበኩላቸው ሕዝቡ ከባለፉት የምርጫ ሂደቶች ተሞክሮ በመውሰድ በዘንድሮው ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ማድረጉን ጠቁመዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የድህረ-ምርጫ ውጤትን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ መኾን እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ከምርጫ በኋላ ሰላም፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት እና እኩልነት እንዲሰፍን በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ምርጫው የተቃርኖ ፖለቲካን በማክሰም ለሀገር ዕድገት እና ሉዓላዊነት በጋራ የሚቆምበትን ምኅዳር መፍጠር እንዳለበትም አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018 ዓ.ም #ደብረ_ብርሃን #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ደጀኔ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🇪🇹🗳️ “ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን” አብን
Next article“ምርጫው የዴሞክራሲ ልምምድን ያየንበት ነው” የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን