የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው የምርጫውን ሂደት መታዘብ ችለዋል።

6

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው የምርጫውን ሂደት መታዘብ መቻላቸውን አስታወቀ።

ኅብረቱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የእኩለ ቀን የትዝብት ሪፖርት ግኝቶች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኅብረቱ የቦርድ ሰብሳቢ ሳህለሥላሴ አበበ፤ ኅብረቱ ለምርጫው ያሰማራቸውን ታዛቢዎች የእኩለ ቀን ሪፖርት በንባብ አሰምተዋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ በመግለጫቸው፤ ሕብረቱ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 2ሺህ 258 ተቀማጭ እንዲሁም 891 ተንቀሳቃሽ በድምሩ 3ሺህ 149 ታዛቢዎች አሰማርቷል፡፡

ታዛቢዎቹ በ 2 ሺህ 258 የምርጫ ጣቢያዎች መሰማራታቸውንም ጨምረው ጠቁመዋል።

በኅብረቱ ትዝብት መሰረት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ የቦርዱ ማህተም፣ የማይለቅ የጣት ቀለም፣ የድምፅ መስጫ ማሸጊያዎች፣ የመራጮች መዝገብ፣ የቦርዱ ድምጽ መስጫ ሳጥኖችን ጨምሮ የምርጫ ቁሳቁሶች መሉ በመሉ ተሟልቷል ብለዋል።

ከተቀበሏቸው ሪፖርቶች መካከል ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው መታዘብ መቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡

#ኢትዮጵያ🇪🇹 እየመረጠች ነው!

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🇪🇹🗳️ በካርዳችን መፃኢ ዕድላችንን ይወስናል ያልነውን ፓርቲ በነጻነት መርጠናል” የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች
Next article“ኢትዮጵያውያን መብታቸውን በአግባቡ እየተጠቀሙ ነው” የአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ቡድን