🇪🇹🗳️ በካርዳችን መፃኢ ዕድላችንን ይወስናል ያልነውን ፓርቲ በነጻነት መርጠናል” የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች

5

 

ደብረታቦር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጠናክሮ በቀጠለበት በደብረ ታቦር ከተማ፣ ነዋሪዎች ምርጫውን በነጻነት እያካሄዱ እንደኾነ ገልጸዋል።

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ገቢያነሽ ጥላሁን ሕዝብ እና ሀገር ያለ መንግሥት መኖር ስለማይችሉ በድምፃቸው ሀገር ለማጽናት የሚበጅ ምርጫ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የምርጫ ሂደቱ ፍትሐዊ እና በሥርዓት የተመራ መኾኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ገቢያነሽ በጦርነት እና በጉልበት የሚመጣ ለውጥ ባለመኖሩ ሰላምን ለማምጣት በምርጫ መሳተፍ ወሳኝ መኾኑን አስገንዝበዋል።

ሌላኛው ድምጽ ሰጭ አቶ ሸጋው አያሌው በበኩላቸው የምርጫ ሂደቱ መልካም እንደነበር እና ለሚፈልጉት ፓርቲ በራሳቸው ፈቃድ ድምጽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ምርጫ ሀገርን ከጦርነት እና ከችግር እንደሚያወጣ በመረዳት በካርዳቸው የወደፊት ዕድላቸውን መወሰን መቻላቸውንም ተናግረዋል። ሕዝቡ በቀሩት ሰዓታት ወደ ጣቢያዎች በመሄድ ድምጹን እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

በደብረ ታቦር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የምርጫ ሂደት ላይ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የቅርብ ምልከታ እያደረጉ ነው።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ደብረ_ታቦር #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ማኅበረሰቡ ያለ ማንም ቀስቃሽ እየመረጠ ነው” ታዛቢ
Next articleየኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው የምርጫውን ሂደት መታዘብ ችለዋል።