
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ክልል ምርጫ ጣቢያ ጣና 02 አሥተባባሪው ዳዊት ዓለሙ ከ12:00 ጀምሮ ማኅበረሰቡ ያለምንም ቀስቃሽ እየመረጠ መኾኑን ገልጸዋል።
ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ እየተሠጠ እንደኾነም አይተናል ብለዋል።
ሌላኛው በባሕር ዳር ምርጫ ክልል ፋሲሎ 03 ምርጫ ጣቢያ 2 ሀ-1 የምርጫ ሂደቱን እየታዘቡ ያገኘናቸው ኡስማን ያሲን እርሳቸው ባሉበት ምርጫ ጣቢያ መራጮች በንቃት እየተሳተፉ እንደኾነ ትዝብታቸውን ነግረውናል።
መራጮች ነጻ ኾነው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ በሰላማዊ መንገድ እየመረጡ እንደኾነ ነው የተናገሩት።
እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት በሚቀጥለው የምርጫ ሂደት በንቃት መታዘባቸውን እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
#election2026 #በምርጫ-ብቻ
#Ethiopian-electio #ኢትዮጵያ-ትመርጣለች
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
