
እንጅባራ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የፈንድቃ ከተማ መራጮች ተናግረዋል።
ፈንድቃ 01 የምርጫ ጣቢያ ላይ ሲመርጡ ያገኘናቸው መራጮች በጥዋቱ ወጥተን በመምረጣችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል። የሚበጅን መምረጥ ለነገይቱ ኢትዮጵያ መሠረት እንደኾነም ገልጸዋል።
በፈንድቃ 02 ምርጫ ጣቢያ ሲመርጡ ያገኘናቸው መራጮችም ሀገራዊ ኀላፊነታችን በመወጣታችን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።
ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ሰለሞን ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
