
አዲስ አበባ: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ድምፃቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ የምርጫ ውጤትን በፀጋ መቀበል ከሠለጠነ ማኅበረሰብ የሚጠበቅ ተግባር መኾኑን ገልጸዋል።
መራጮቹ የምርጫ ካርድ ከማውጣት ጀምሮ ድምፃቸው ያለውን ዋጋ በመረዳት የፓርቲዎችን አማራጭ ፖሊሲዎች በምርጫ ክርክር ወቅት ሲከታተሉ መቆየታቸውን እና ዛሬ በማለዳ ተገኝተው ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ውጤቱ ይፋ ሲደረግ በሰላማዊ መንገድ በመቀበል ሀገርን ለሚያሥተዳድረው አካል ዕድል መስጠት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ለሀገር የዴሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት ምርጫ ወሳኝ መኾኑን የጠቀሱት መራጮቹ በምርጫ ሀገረ መንግሥትን የመመሥረት ልምምድ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
