🇪🇹🗳️ “እኔ አካል ጉዳተኛ ብኾንም የተሰጠኝን መብት ተጠቅሜ በቀዳሚነት መርጫለሁ”

8

 

ደብረብርሃን: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሽዋ ዞን በመሀል ሜዳ ምርጫ ክልል በማለዳው የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን የሰጡት ሀምሳ አለቃ ከፈለኝ ጥላሁን “እኔ አካል ጉዳተኛ ብኾንም የተሰጠኝን መብት ተጠቅሜ በቀዳሚነት መርጫለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።

አካል ጉዳተኞች ሕገ-መንግሥቱ ያረጋገጠላቸውን ዴሞክራሲያዊ መብት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው የሚያምኑት ሀምሳ አለቃ ከፈለኝ ይህ ዕድል ከአምስት ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ እና ሕዝቡ ይመራኛል የሚለውን አካል የሚመርጥበት በመኾኑ ሁሉም ዜጋ ድምፁን ሊሰጥ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አካል ጉዳተኛ ከኾኑ ወዲህ ለ3ኛ ጊዜ ድምፃቸውን እየሰጡ መኾናቸውን የጠቀሱት ሀምሳ አለቃው ከፈለኝ በምርጫው ሂደት ወቅት በማኅበረሰቡ ዘንድ የታየው መረዳዳት፣ ትብብር እና አካታችነት በእጅጉ እንዳስደሰታቸውም አክለው ገልጸዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ደብረ_ብርሃን #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleነብሰ ጡርነት ያልበገራቸው መራጭ እናቶች በኮምቦልቻ ከተማ።
Next articleለዴሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት ምርጫ ወሳኝ ነው።