
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኮምቦልቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ አየር ማረፊያ ቀበሌ አየር ማረፊያ ምርጫ ጣቢያ ያገኘናቸው ነብሰ ጡር እናቶች ድምጻቸውን ለመስጠት ተገኝተዋል።
በምርጫ ሕጋዊ መንግሥትን መመሥረት የእናቶች ጤና እንዲጠበቅ እና ለእናቶች አገልግሎት የሚሰጡ ጤና ተቋማት እንዲበራከቱ ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
ድምጻቸውን ለመስጠት በምርጫ ጣቢያ በመገኘታቸው ደስተኛ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ድምጻቸውን በመስጠታቸው ለቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊ ሀገርን ለማሸጋገር እንደሚያግዝም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
