ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ መኾኑን የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ገለጹ።

8
🗳️
ደብረብርሃን፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የአርጎባ አንድነት ጀበርቲን ፓርቲን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎች በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
‎የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩት ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ ‎፤ እሳቸው በሚወዳደሩበት አካባቢ ሂደቱ ሰላማዊ በኾነ መልኩ እየተከናወነ እንደኾነ ተናግረዋል።
‎በተመሳሳይ የአርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተወዳደሩ የሚገኙት ሀያት ኡስማን በሰጡት አስተያየት የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ በኾነ መልኩ እየተካሄደ መኾኑን መታዘባቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የምርጫ ጣቢያዎችን ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው።
Next articleነብሰ ጡርነት ያልበገራቸው መራጭ እናቶች በኮምቦልቻ ከተማ።