ደብረብርሃን: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በደብረብርሃን ከተማ ድምፃቸውን ከሰጡት መካከል የ95 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ ጋሽ ብዙነህ መሐመድ አንዱ ናቸው።
እኝህ አባት ዕድሜያቸው ሳይበግራቸው ወደ ምርጫ ጣቢያ ያቀኑት የምርጫ እና የመሪ አስፈላጊነት በጥልቅ በመረዳታቸው ነው።
”እኔ እምመርጠው ጠባቂ እንዲኖረኝ ነው” ብለዋል፡፡
ጋሽ ብዙነህ ድምፃቸውን በካርዳቸው ከሰጡ በኋላ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ለሀገር ዕድገት እና ለሰላም በትጋት እንዲቆሙ አባታዊ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ደጀኔ በቀለ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
