“ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠብሣቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ

9
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል። ዜጎችም ድምጻቸውን እየሰጡ ነው። የእስካሁኑን የድምጽ አሰጣጥ አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠብሣቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ከጠዋት ጀምሮ ምርጫው እየተካሄደ መኾኑን ተናግረዋል። ቦርዱ ከምርጫው አስቀድሞ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን መሥራቱንም አንስተዋል።
ከ350 ሺህ በላይ የምርጫ አሥፈጻሚዎችን ማሠማራቱንም ገልጸዋል።
ምርጫው ነጻ እና ገለልተኛ እንዲኾን ታዛቢዎች በምርጫ ጣቢያዎች መገኘታቸውንም አንስተዋል።
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ
#Ethiopian-electio #ኢትዮጵያ-ትመርጣለች
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“ሕጋዊ መንግሥትን መመሥረት የሚቻለው በምርጫ ብቻ ነው” ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች
Next articleምርጫ አለመግባባቶችን በሠለጠነ መንገድ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል መሳሪያ ነው።