ምርጫ አለመግባባቶችን በሠለጠነ መንገድ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል መሳሪያ ነው።

8
🇪🇹🗳️ፍኖተሰላም: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በፍኖተ ሰላም ከተማ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎች የድምጽ መስጠት ሂደቱ ሰላማዊ መኾኑን ገልጸዋል።
ወጣት አምበሉ ቢያድግልኝ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጹን በነጻነት መስጠቱን ተናግሯል።
ሂደቱ ነጻ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ መኾኑንም አብራርቷል። ምርጫ አለመግባባቶችን በሠለጠነ መንገድ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል መሳሪያ መኾኑንም ተናግሯል።
መምረጥ መብት እና ሀገርን ወደ ልማት የሚያሸጋግር መልካም ተግባር በመኾኑ ወጣቶች ምርጫውን በሰላም አጠናቅቀው ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የልማት ምዕራፍ ሊወስዷት እንደሚገባም አስገንዝቧል።
ሃምሳ አለቃ አዱኛ ዓለማየሁ ሀገር ሊኖር የሚችለው ሕዝብን የሚያሥተዳድር መሪ ሲኖር ነው ብለዋል። እያንዳንዱ ዜጋም መሪውን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት እንዳለው አብራርተዋል። መራጮች በነጻነት ድምጻቸውን እየሰጡ መኾኑን መታዘባቸውንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠብሣቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ
Next article“ምርጫ ለአንድ ሀገር የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ነው” የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች