የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዲሱን የደንብ ልብስ አስተዋወቀ።

4

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ባለፋት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የደንብ ልብስ በአዲስ የደንብ ልብስ መተካቱን አስታውቋል። አዲሱን የደንብ ልብስም ዛሬ በልዩ ልዩ ፖሊሳዊ ሥርዓት አስተዋውቋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር) አዲሱ የደንብ ልብስ በፖሊስ ሠራዊት ተወዳጅ የኾነ ልብስ ነው ብለዋል።

በነበረው የጸጥታ ችግር ብዙ አይነት ልብሶች እንደነበሩ ጠቁመዋል። አሁን ላይ ደረጃውን የጠበቀ የደንብ ልብስ ተዘጋጅቶ ለኅብረተሰቡም በሥርዓቱ መሠረት ማስተዋወቁን ገልጸዋል።

የደንብ ልብሱ የፖሊስ ሠራዊቱ ከ15 ዓመታት በፊት ሲጠቀምበት የነበረውን ልብስ መሠረት ያደረገ መኾኑንም አንስተዋል።

አዲሱ የደንብ ልብስ በኅብረተሰቡም ተወዳጅ የነበረ መኾኑን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት የነበረውን የደንብ ልብስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመተካቱ ሂደትም የሪፎርሙ አካል መኾኑን ነው የተናገሩት።

በሁሉም የፖሊስ መምሪያዎች እና ፖሊስ ጽሕፈት ቤቶች ሥርዓቱን ጠብቆ ትውውቅ እየተደረገ ወደ ሥራ እየገባ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

#የአማራ_ክልል_ፖሊስ #የደንብ_ልብስ #የፖሊስ_ሪፎርም AmharaPolice #NewPoliceUniform

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

Previous articleበሰሜን ሸዋ ዞን በጽንፈኛው ቡድን ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
Next articleየምክክር ጉባዔው ስኬታማ እንዲኾን የአወያዮች ሚና ከፍተኛ ነው።