
#ባሕር_ዳር: ሰኔ 25/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በጽንፈኛው ቡድን ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።
በመከላከያ ሠራዊት የአየር ወለድ ክፍለ ጦር ሬጅመንት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ወረዳ በልዩ ስሟ ራራት ማርያም በምትባል ቀበሌ ውስጥ እየተሸሎከለከ ሕዝብ ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የቆየውን ጽንፈኛ ቡድን መደምሰሱን አስታውቋል።
ሠራዊቱ ጽንፈኛውን በመደምሰስ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያዎችን መማረኩን የመብረቅ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል በርሄ ገብረትንሳኤ ተናግረዋል።
ሠራዊቱ የሕዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማረጋገጥ እያደረገ በሚገኘዉ ጠንካራ ስምሪት ጽንፈኛዉ ቡድን ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ የተለያዩ መሣሪያዎችን ፣ ተተኳሾችን እና ሌሎች ቁሳቁስ መማረክ መቻሉን ገልጸዋል። በርካታ የጽንፈኛው ኀይል መደምሰሳቸውንም አንስተዋል።
ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ቡድኑ አሁን ላይ በተወሰደበት ጠናካራ እርምጃ አቅሙ ከቀን ወደ ቀን እየተዳከመ መምጣቱን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
