የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዋና የሂደት መገለጫዎች!

3

 

#ባሕር_ዳር ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት አሳታፊነትን እና አካታችነትን ለማረጋገጥ ምን ምን ተግባራትን አከናወነ?

☀️ ሰፊ የኅብረተሰብ ተሳትፎ፦
ምክክሩን አሳታፊ ለማድረግ የሃይማኖት ተቋማትን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ ነበር።

☀️ ሁለንተናዊ ተደራሽነት፦
በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በመንቀሳቀስ አጀንዳዎችን የመሰብሰብ እና ወካይ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ ተሰርቷል።

☀️ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተካፋይነት፦
ሀገር ሽማግሌዎች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ምሁራን፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ሠራተኞች እና ተፈናቃዮች በእኩልነት እንዲሳተፉ ተደርጓል።

☀️ የዳያስፖራ ተሳትፎ፦
የምክክር ሂደቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም ያሳተፈ ነው።

☀️ ታሪካዊ የውይይት መድረክ፦
አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ከሊቃውንትና ከመሪዎች ጋር በአንድ መድረክ ተቀምጠው ስለ ሀገራቸው የሚወያዩበት ዕድል ተፈጥሯል።

☀️ የአጀንዳዎች ምንጭ፦
የኮሚሽኑ ስምንቱ ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች በቀጥታ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት፣ ስጋት እና ተስፋ የተቀዱ ናቸው።

☀️ ለወደፊት የተቀመጠ ግብ፦
ኮሚሽኑ አሁን ካለው ዝግጅት በኋላ፣ በሰፊው ለመምከር ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም ቀጠሮ በመያዝ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

#አሚኮ #የኢትዮጵያ_ሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን #ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው

Previous articleበአማራ ክልል የንጹሕ መጠጥ ውኃ ሽፋን 79 ነጥብ 91 በመቶ ደርሷል።
Next articleበሰሜን ሸዋ ዞን በጽንፈኛው ቡድን ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።