የምክክር ጉባዔው ስኬታማ እንዲኾን የአወያዮች ሚና ከፍተኛ ነው።

3

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባዔው ሙያዊ ማብራሪያ ከሚያቀርቡ ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ በአካታች እና በአሳታፊ መርሕ ሀገራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ ሢሠራ ቆይቷል ብለዋል።

ከመላው ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 300 ወረዳዎች የልዩነት ትርክቶችን ለማረም አጀንዳዎችን አሰባስቧል፤ ከእነዚህ አካባቢዎች የተውጣጡ 4 ሺህ ተሳታፊዎችን በመምረጥ ስለሀገራቸው እንዲመክሩ አጀንዳዎች ተለይተዋል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ሥላሴ በተመረጡት ስምንት አጀንዳዎች ላይ ተወያዩች መሠረታዊ ዕውቀት ኖሯቸው ለሀገር እና ለሕዝብ የሚጠቅም ሀሳብ እንዲያመነጩ ሙያዊ ማብራሪያ የሚያቀርቡ ባለሙያዎች ሚናቸው ከፍተኛ መኾኑን አንስተዋል።

ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ እያንዳንዱ 500 ሰዎችን በሚይዝ ስምንት ቡድኖች ተከፋፍሎ እንደሚደረግ የገለጹት ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ጥልቅ ምክክር እንዲያደርጉም አሳስበዋል። አወያዮች በገለልተኝነት ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፎችን እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሙያዊ ማብራሪያ የሚያቀርቡ ባለሙያዎችም ገለልተኛ ሙያዊ ትንታኔን በማቅረብ ለምክክሩ ውጤታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

#ሀገራዊምክክር #ምክክርጉባኤ #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ቤተልሔም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዲሱን የደንብ ልብስ አስተዋወቀ።
Next articleበዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።