በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።

4

 

#ባሕር_ዳር: ሰኔ 25/2018 ዓ.ም በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የግጭትን መዘዝ የተረዱ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።

ሰላም የሕይወት መሠረት ነው። የሰላምን አስፈላጊነት እና የግጭትን መዘዝ የተረዱ በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ እየተቀበሉ ይገኛሉ።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጌታወይ አብርሃ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በ2018 ዓ.ም በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ የተሃድሶ ሥልጠና እንዲወስዱ በማድረግ፤ ወደ ቀድሞ ሥራቸው በመመለስ፤ በተለያዩ የሥራ መስኮች እንዲሠማሩ በማድረግ መልሶ ማቋቋም እንደተቻለም ተናግናዋል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የጸጥታ አካላት የአካባቢውን ሰላም ለማጽናት በቁርጠኝነት እየሠሩ ነው ብለዋል። ከማኅበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደኾነም አንስተዋል።

ማኅበረሰቡ የሰላምን አማራጭ የሚቀበሉ ታጣቂዎችን በመቀበል እና ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው ብለዋል። በብሔረሰብ አሥተዳደሩ አንጻራዊ ሰላም መኖሩንም ገልጸዋል።

ሕገወጡ የሕወሃት ቡድን የሚፈጽመውን ትንኮሳ የጸጥታ ኃይሉ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመኾን እያከሸፈ መኾኑን እና ሰላምን ለማጽናት እየሠራ እንደኾነም ጠቁመዋል።

#አሚኮ_ዜና# ዋግኽምራ ብሔረሰብ#ሰላም#አማራ ክልል#ኢትዮጵያ 🇪🇹

#WagHimra #Peace #Ethiopia🇪🇹#Amhara

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየምክክር ጉባዔው ስኬታማ እንዲኾን የአወያዮች ሚና ከፍተኛ ነው።