“ሕጋዊ መንግሥትን መመሥረት የሚቻለው በምርጫ ብቻ ነው” ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

5
ደሴ: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ አንድ ምርጫ ክልል እየተወዳደሩ የሚገኙ የግል ተወዳዳሪ እና የተፎካካሪ ፓርቲ እጩዎች ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
በቁጠባ ቀበሌ ሸሻበር ቁጥር ሁለት የምርጫ ጣቢያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል ተወዳዳሪ እጩ ዶክተር ሀሰን ይመር በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ወጥቶ እየመረጠ መኾኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በጠመንጃ ሳይኾን በምርጫ ሂደት ሕጋዊ መንግሥትን ለመመሥረት ሕዝቡ እየመረጠ መኾኑንም መታዘባቸውን ተናግረዋል።
በቢራሮ ክፍለ ከተማ ሦስት መዋለ ሕጻናት ምርጫ ጣቢያ የነጻነት እና ዕኩልነት ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ኑርየ እብሬ በምርጫ ሂደቱ ማኅበረሰቡ እያሳየ የሚገኘው ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በሀሰን ሀገር ክፍለ ከተማ በሚሊኒየም ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ሲሰጡ ያገኘናቸው የኢዜማ ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ይማም በላይ ምርጫው በዴሞክራሲያዊ መንገድ እየተካሄደ መኾኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
#Ethiopian-electio #ኢትዮጵያ-ትመርጣለች
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article🇪🇹🗳️ በጎንደር መንታ ሕጻናት ልጆችን ታቅፈው ድምጽ የሰጡ እናት።
Next article“ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠብሣቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ