🇪🇹🗳️ በጎንደር መንታ ሕጻናት ልጆችን ታቅፈው ድምጽ የሰጡ እናት።

7

 

ጎንደር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠታቸውን ቀጥለዋል። በጎንደር ከተማ መድን ምርጫ ጣብያ አሚኮ ያገኛቸው ወይዘሮ ማስተዋል አበራ ሁለት መንታ ልጆቻቸውን ይዘው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ወይዘሮ ማስተዋል እንደገለጹት ምንም እንኳን ሁለት መንታ ልጅ ታቅፎ ለምርጫ መሰለፍ አድካሚ ቢኾንም በምርጫው ድምጻቸውን መስጠት ከግል ድካም በላይ ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

ሌላኛዋ ሁለት ሕፃናት ልጆችን ታቅፈው ድምጽ የሰጡት እናት ወይዘሮ ፀሐይ ረታ ምርጫው ለሕጻናት ልጆቻቸው የሚበጅ፣ ለነገው እጣፋንታ ወሳኝ መኾኑን በመገንዘብ ድምጻቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች እናቶችም ድካም ሳይበግራቸው ልጅ በእቅፍ ይዘው እየመረጡ ነው።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ጎንደር #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🇪🇹🗳️ የዳንግላ ወረዳ አርሶ አደሮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
Next article“ሕጋዊ መንግሥትን መመሥረት የሚቻለው በምርጫ ብቻ ነው” ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች