🇪🇹🗳️ ዜጎች በምርጫ መንግሥት ለመመስረት ያላቸው ቁርጠኝነት የሚደነቅ መኾኑን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ።

38

 

ጎንደር፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎‎በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክል ድንጋይ ከተማ ምርጫው ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እየተካሄደ ነው። በምርጫው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች
ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
‎
‎በትክል ድንጋይ ከተማ በቀበሌ 01 ምርጫ ጣቢያ “ሐ” ድምጽ ሲሰጡ ያገኘናቸው የቅማንት ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ተገኑ ደረጀ ምርጫው ሰላማዊ እና ፍተሐዊ በኾነ መንገድ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
‎
‎በከተማው ባሉ ምርጫ ጣቢያዎች ምልከታ ማድረጋቸውን የተናገሩት እጩው ዜጎች በድምፃቸው መንግሥት ለመመስረት ያላቸውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
‎
‎ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
‎
‎ፓርቲያቸው ሕዝብ የሚሰጠውን ድምጽ በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ መኾኑንም ገልጸዋል።
‎
‎ምርጫው ሰላማዊ በኾነ መንገድ እየተካሄደ መኾኑን መታዘባቸው የተናገሩት ደግሞ የኢዜማ ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ መምህር አማረ በየነ ናቸው።

የተሻለ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ፍትሐዊ ምርጫን ባሕል ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ቤተልሄም አዱኛ ምርጫው በወረዳው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደኾነ ተናግረዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #ጎንደር #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ:- አዲስ ዓለማየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article
Next article🇪🇹🗳️ የዳንግላ ወረዳ አርሶ አደሮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።