
ካርዳቸውን አባ ሳሙኤል ቀበሌ አየር ማረፊያ ምርጫ ጣቢያ ማውጣታቸውን የገለጹት አቶ መኮንን ድምጻቸውንም በዚሁ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በተገኙበት የምርጫ ጣቢያ መራጮች ከማለዳው ጀምሮ ይበጀናል፣ ያስተዳድረናል ያሉትን እየመረጡ መኾናቸውን አንስተዋል።
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ በኾነ መንገድ እየተከናወነ መኾኑን መታዘባቸውንም አመላክተዋል።
ምርጫ ሰላማዊ መንግሥት ለመመስረት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነውም ብለዋል። መራጩ ሕዝብ የሰጠውን ድምጽ በጸጋ ተቀብሎ የዴሞክራሲ ሥርዓትን መለማመድ ይገባልም ነው ያሉት።
ሀገርን ለማስቀጠል ኀላፊነትን መወጣት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል። ሕዝብ የሰጠውን ድምጽ መቀበል አማራጭ ብቻ ሳይኾን ግዴታ መኾኑንም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ደስታ ካሣ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
