
ደብረ ብርሃን፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ 08 ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ከሰጡ መራጮች መካከል ወይዘሮ ዘውዴ መኮንን አንዷ ናቸው።
የዛሬው አሻራቸው ለራሳቸው ብቻ ሳይኾን ለልጆቻቸው ትልቅ ትርጉም እንዳለው በጽኑ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
”በምርጫው መሳተፍ ለእኔም፣ ለልጆቼም፣ ለሀገሬም የማይተካ ሚና አለው ብለዋል። በተለይም ለልጆቼ ሰላሟ የተጠበቀ ሀገር ለማስረከብ የዛሬው ድምጼ ትልቅ ዋጋ አለው” ነው ያሉት።
ምርጫ የዜግነት መብት ብቻ ሳይኾን ለትውልድ የሚቀመጥ የተስፋ መሠረት ጭምር ነው ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ቀለሟ ስመኝ ናቸው።
እናቶች ለልጆቻቸው የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ዛሬ ላይ ድምጻቸውን እንዲሰጡም መክረዋል።
#Ethiopian-electio #ኢትዮጵያ-ትመርጣለች
ዘጋቢ፦ ደጀኔ በቀለ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
