ምርጫውን አፍሪካውያን መታዘባቸው ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ፈር ቀዳጅነቷን ዳግም በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የደገመችበት ነው።

8
🇪🇹🗳️አዲስ አበባ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 17 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ እና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር እናታለም መለሰ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ሚኒስትሯ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም መምረጣቸውን ገልጸዋል።
የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጠት ሂደት ነፍሰጡሮች፣ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሌሊት ጀምሮ ለሀገር ቅድሚያ በመስጠት በንቃት እየተሳተፉበት የሚገኝ ምርጫ ነው ብለዋል።
ሂደቱን አፍሪካውያን ታዛቢዎች እና የሲቪክ ማኅበራት እየተከታተሉት መኾኑን ሚኒስትሯ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የፓንአፍሪካኒዝም ፈር ቀዳጅነቷን ዳግም በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የደገመችበት ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ኢብራሂም መሃመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“መብቴን ተጠቅሜ መምረጤ ለሀገሬ ያለኝን ፍቅር ማሣያ ነው” አካል ጉዳተኛው መራጭ
Next article“የዛሬው አሻራችን ለራሳችን ብቻ ሳይኾን ለልጆቻችንም ትልቅ ትርጉም ያለው ነው” እናቶች