ኢትዮጵያ የተሳካ COP32 ለማካሄድ ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት አላት።

3

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ. ር) በUNFCCC ስር የአረብ ቡድን አባል ሀገራት የልዑካን መሪዎች ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ንግግር አድርገዋል።

በስብሰባው ወቅት አባላቱ በኢትዮጵያ አመራር እና በCOP32 ሂደት ላይ የተመራጭ ፕሬዝዳንቱ በሚያሳዩት መሪነት ላይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና በአረብ ቡድን አባል ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ እና ጠንካራ ግንኙነት ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ. ር) ኢትዮጵያ ከሁሉም ተዋዋይ አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት የተሳካ COP32 ለማካሄድ ያላትን ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት ለቡድኑ አረጋግጠዋል።

#COP31 #EthiopiaCOP32 #ClimateAction

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_02_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ለትውልድ እየተሸጋገረ መኾኑ የታየበት የዳካሩ የታዳጊዎች ድል!