“ለሀገር ዕድገት እና ልማት ስንል በምርጫው ተሳትፈናል” መራጮች

7
🇪🇹🗳️ደብረማርቆስ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን አምበር ከተማ ድምጽ ሲሰጡ ያገኘናቸው አዛውንት እማሆይ ይፍቱ ዳኘው የ74 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ናቸው።
ከዚህ በፊት በሁለት የምርጫ ጊዜያቶች መሳተፋቸውንም ገልጸዋል። በዛሬው ምርጫ ለቀጣዩ ትውልድ የሚበጅ መንግሥትን ለመምረጥ በምርጫው መሳተፋቸውንም ነው የተናገሩት።
ሌላው በምርጫው ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው አቶ ምናለ ታረቀኝ አካል ጉዳተኛ መኾናቸው ምንም ሳይገድባቸው ይኾነኛል እና ያስተዳድረኛል የሚሉትን ለመምረጥ በምርጫ ጣቢያ መገኘታቸውን ተናግረዋል።
በምርጫው ለአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ስል ድምጼን ሰጥቻለሁም ብለዋል።
ሌሎች አካል ጉዳተኞችም ያወጡትን ካርድ በመጠቀም የሚበጃቸውን መምረጥ እንዳለባቸው ነው የተናገሩት።
ማኅበረሰቡ በምርጫው ከመሳተፍ ባለፈ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ መሥራት እንደሚገባውም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየ95 የዕድሜ ባለጸጋው በምርጫው ድምጻቸውን ሰጡ።
Next article“ምርጫ መሪህን በሰላም የምትመርጥበት መንገድ ነው” የ90 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ