የ95 የዕድሜ ባለጸጋው በምርጫው ድምጻቸውን ሰጡ።

7
🇪🇹🗳️ፍኖተሰላም፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
ከእነዚህ መራጮች መካከል ከ95 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ጴጥሮስ ዋነኛው አንዱ ናቸው። ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ላይ መሳተፋቸውንም አስታውሰዋል።
በዘንድሮው ምርጫ በመሳተፋቸው እና የሚያምኑበትን በመምረጣቸው ደስተኛ መኾናቸውን ገልጸዋል። የዕድሜ ባለጸጋው ያመኑበትን አካል መምረጣቸውንም ተናግረዋል።
ምርጫ የሕዝብን ዕውነተኛ ውሳኔ ለማሳየት እና ለማወቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። ዜጎች በምርጫ በመሳተፍ የዜግነት መብታቸውን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article”በሀገር ላይ ድርሻ ስላለን የምንፈልገውን ፓርቲ መርጠናል” አካል ጉዳተኞች
Next article“ለሀገር ዕድገት እና ልማት ስንል በምርጫው ተሳትፈናል” መራጮች