“በጠብመንጃ ሳይኾን በምርጫ ብቻ መንግሥት እንደሚመሠረት በመረዳቴ ድምፄን ሰጥቻለሁ” የሰላም አማራጭን የተቀበለ ወጣት

11
🇪🇹🗳️
ከሚሴ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በከሚሴ ከተማ ድምጹን ለሚበጀው ሲሰጥ አሚኮ ያገኘው የሰላም አማራጭን የተቀበለው ወጣት መሀመድ አማን፤ ከዚህ ቀደም በትጥቅ ትግል ውስጥ እንደነበር ገልጿል።
አሁን ላይ የመንግሥትን እና የሕዝብን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም መምጣቱን የገለጸው ሙሀመድ አማን በ7ኛው ጠቅላላ መርጫ በሰላማዊ መንገድ መምረጡን ጠቁሟል።
መንግሥት መመሥረት የሚቻለው በጠብመንጃ ሳይኾን በምርጫ ካርድ ብቻ መኾኑን በመገንዘቤ ካርድ በማውጣት ይበጀኛል ላልኩት ድምጼን ሰጥቻለሁ ብሏል።
ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ለ7ኛ ጊዜ በመምረጥ ታሪክ አስቀምጫለው” መራጭ
Next article”በሀገር ላይ ድርሻ ስላለን የምንፈልገውን ፓርቲ መርጠናል” አካል ጉዳተኞች