“ለ7ኛ ጊዜ በመምረጥ ታሪክ አስቀምጫለው” መራጭ

9
🇪🇹🗳️
ደብረብርሃን፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቡልጋ ከተማ አሥተዳደር 02 ምርጫ ጣቢያ የተገኙት አቶ ሲሳይ በየነ “መንግሥት በምርጫ መመሥረት እና መጽናት አለበት” በሚል ጽኑ ዕምነት ለ7ኛ ጊዜ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ያስተዳድረኛል ያሉትን አካል በነፃነት የመምረጥ ልዩ መብታቸውን ለመጠቀም አስቀድመው ያለምንም ጎትጓች ካርድ ማውጣታቸውንም ገልጸዋል፡፡
“በምርጫ ጣቢያው የተመለከትኩት የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ የድምጽ አሰጣጥ እጅግ አስደስቶኛል” ብለዋል።
ለሰባት ተከታታይ የምርጫ ዘመናት ያሳዩት ይህ የማይነጥፍ ቁርጠኝነት በዴሞክራሲያዊ መንገድ መሪን የመምረጥ ጽኑ አቋም ስላላቸው መኾኑን አቶ ሲሳይ ጠቁመዋል፡፡
ይህንን ልዩ ሀገራዊ አሻራቸውን በነፃነት ድምጻቸውን እንደሰጡ የገለጹት እኚህ መራጭ በሂደቱ ላይ ደስተኛ እንደኾኑ ተናግረዋል፡
ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ድምጼን የሰጠኹት ለሀገር ሰላም ነው” የዕድሜ ባለጸጋዋ እናት
Next article“በጠብመንጃ ሳይኾን በምርጫ ብቻ መንግሥት እንደሚመሠረት በመረዳቴ ድምፄን ሰጥቻለሁ” የሰላም አማራጭን የተቀበለ ወጣት