“ድምጼን የሰጠኹት ለሀገር ሰላም ነው” የዕድሜ ባለጸጋዋ እናት

8
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ ፋርጣ አንድ ምርጫ ክልል ነዋሪዎች ድምጽ እየሰጡ ነው።
ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች እና አረጋውያን በምርጫው እየተሳተፉ ነው።
በከተማዋ ሁለት ምርጫ ጣቢያ ውኃ አገልግሎት “ለ” አንድ ላይ ድምፅ ሲሰጡ ያገኘናቸው የእድሜ ባለጸጋዋ ወይዘሮ አሰፉ ደርሴ በሌሊት ቤተ ክርስቲያን ደርሰው እግረ መንገድ ድምፅ ለመስጠት መምጣታቸውን ነግረውናል። መራጯ ቤተ ክርስቲያን ሄጄ የፀለይኩት ለሀገር ሰላም፣ ድምፄን የሰጠኹትም ለሀገር ሰላም ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ በምርጫ መሳተፋቸውን የነገሩን አዛውንቷ “ከብት ያለ እረኛ፣ ሰው ያለ ዳኛ አይኖርም ብየ ዘንድሮም የሚበጀውን መርጫለሁ” ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለ7ኛ ጊዜ በምርጫ የሚሳተፉት የዴሞክራሲ ሕያው ምስክር እናት።
Next article“ለ7ኛ ጊዜ በመምረጥ ታሪክ አስቀምጫለው” መራጭ