ልጃቸውን ለመገላገል በምጥ ስሜት ውስጥ ኾነው ድምጽ የሰጡት እናት።

8
🇪🇹🗳️
ከሚሴ፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ሳራ አህመድ በከሚሴ ከተማ የመተሆሮ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።
ወይዘሮ ሳራ ልጃቸውን ለመገላገል የምጥ ስሜት እየተሰማቸው ምጣቸውን ተቋቁመው ለሀገር ይበጃል ላሉት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ሀገር እና ትውልድን ለማስቀጠል በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ያስፈልጋል ያሉት ወይዘሮ ሳራ።
ድምጻቸውን ለሚወክላቸው በመስጠታቸው ደስተኛ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላም ልጃቸውን ለመገላገል በመጡበት አምቡላንስ ወደ ከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል አቅንተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ይበጀናል” የሚሉትን በነጻነት እየመረጡ መኾናቸውን የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleለ7ኛ ጊዜ በምርጫ የሚሳተፉት የዴሞክራሲ ሕያው ምስክር እናት።