ምርጫ የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ መኾኑን የጎንደር ከተማ መራጮች ተናገሩ።

10
🇪🇹🗳️
ጎንደር፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጠዋት ወጥተው ይበጀናል ላሉት ድምፃቸውን መስጠታቸውን በጎንደር ከተማ የምርጫ ክልል 2 መራጮች ተናግረዋል።
‎አሚኮ ያነጋገራቸው ወይዘሮ ህድጃ ጥጋቡ በጠዋት ወጥተው ይበጀኛል ላሉት ድምፃቸውን መስጠታቸውንም ነው የተናገሩት።
‎ሃሳባቸውን ያጋሩን ሌላኛው መራጭ አቶ መኮንን ተካልኝ ለሀገር ዕድገት ይበጃል ያሉትን መምረጣቸውን አንስተዋል።
‎ካርዳቸውን ተጠቅመው ሰላምን ለማጽናት መምረጣቸውን የነገሩን ደግሞ መሪጌታ ደሴ መኳንንት ናቸው።
‎አስተያየት ሰጭዎቹ በጠዋት ወጥተው በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን መስጠታቸውንም አመላክተዋል።
መራጮቹ ‎ምርጫ የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ መኾኑን በመረዳት ዜጎች ያወጡትን ካርድ በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸውም መክረዋል።
ዘጋቢ፦ደስታ ካሳ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለሰባተኛ ጊዜ በምርጫ የተሳተፉት መራጭ በኮምቦልቻ
Next article“ይበጀናል” የሚሉትን በነጻነት እየመረጡ መኾናቸውን የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።