
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር እና በባሕር ዳር ከተማ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ አረጋ ከበደ በባሕርዳር ከተማ ግሽ ዓባይ በሚገኘው ሕዳሴ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ሕዝቡ በምርጫው ያሳየው የነቃ ተሳትፎ ለምርጫው ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ምርጫ የአንዲት ሀገር የዴሞክራሲ ልምምድ ማሳያ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት መመስረት አስፈላጊ ነው
ብለዋል። ይህም የጸና ሀገረ መንግሥትን እና የዴሞክራሲ ተቋማትን በዘላቂነት ለመገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል።
በቴዎድሮስ ደሴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
