🇪🇹🗳️ ለመምረጥ ከሌሊት 7:00 ጀምረው ሰልፍ የያዙት መራጭ

6

 

አዲስ አበባ፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታደሰ ሽፈራው ይባላሉ። በአዲስ አበባ ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወርዳ 9 ነዋሪ ናቸው። በወረዳ 9 ሼርድ ካምፓስ ለመምረጥ ከተገኙ ዜጎች መካከል አንዱ ናቸው።

ምርጫ የሚያሥተዳድረኝን፣ ይኾነኛል ያልኩትን መንግሥት ለመምረጥ ወሳኝ የዴሞክራሲ ሂደት ነው ይላሉ አቶ ታደሰ።

እናም ዛሬ ለመምረጥ ያወጣሁትን ካርድ ለመጠቀም ከለሊቱ 7:00 ጀምሬ በምርጫ ጣቢያው ተገኝቻለሁ ብለዋል።

አቶ ታደሰ በዚህ ምርጫ ለመሳተፍ ከተገኙ ዜጎች ከፊት ተሰይመዋል። አቶ ታደሰ ታድያ በምርጫ አስሥተባባሪ አካላት ሰዓቱ ገና እንደኾነ ተነግረው ወደ ቤት ቢመለሱም ዳግም ከለሊቱ 11:00 ለመምረጥ መገኘታቸውን ነግረውናል። መምረጣቸውንም ጠቁመዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018_ዓ.ም #አዲስ_አበባ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ቴዎድስ ኀይለኢየሱስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🇪🇹🗳️ “ለሀገሬ ሰላም መርጫለሁ” መራጭ
Next articleበጎንደር ከተማ መራጮች ድምጻቸውን እየሠጡ ነው።