
ፍኖተ ሰላም: ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ተዘጋጅታለች።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ የሚኖሩ አካል ጉዳተኞች በምርጫው ሀገራዊ ኀላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡት አካል ጉዳተኞቹ በሀገረ መንግሥት ምሥረታው የበኩላቸውን ለመወጣት በመጠባበቅ ላይ እንደኾኑ ነው የተናገሩት።
ምርጫው የሀገሪቱን የወደፊት መጻኢ ዕድል የሚወስን መኾኑን በመረዳት ሀገራዊ ኀላፊነታችን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ነው ያሉት።
#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#ፍኖተ-ሰላም #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ:- ንጉሥ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
