
ደብረ ብርሃን: ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሰላሙ በተጠበቀ መልኩ ለመፈጸም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ምክትል ኀላፊ ዓባይ ድሌ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የጸጥታ አባላት ስምሪት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል። የጸጥታ አካሉ በቁርጠኝነት ኀላፊነቱን እየተወጣ እንደኾነም ገልጸዋል።
በምርጫው ዕለት እና በድህረ-ምርጫው ሂደት አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ማኅበረሰቡ የተለመደውን ንቁ ትብብር እና ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#ሰሜን-ሸዋ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
